← Back to Press Center
OTHERSACTIVE2026-11-24

እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ!



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


‎

‎"እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?" (ኢሳይያስ 58፥6–7)


‎

‎ፆመ ነቢያት (የገና ፆም) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ከሚባሉ ሰባት የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን፣ ምዕመናን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በጸሎት፣ በንስሐ እና በመንፈሳዊ ዝግጅት የሚቀበሉበት ታላቅ የበረከት ወቅት ነው። ይህ ፆም በየዓመቱ ኅዳር 15 ቀን የሚጀምር ሲሆን፣ እስከ ታኀሣሥ 29 ቀን ድረስ የሚዘልቅና በታኅሣሥ 29 ቀን በሚከበረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (የገና) በዓል ይፈጸማል።


‎

‎​ፆሙ «ፆመ ነቢያት» ተብሎ የተሰየመበት ዋና ምክንያት የብሉይ ኪዳን ነቢያት የመሲሑን መወለድ እና የሰው ልጅን የማዳን ሥራ አስቀድመው በትንቢት የተናገሩበትን፣ በናፍቆትና በጸሎት የተጠባበቁበትን ዘመን የሚያስታውስ በመሆኑ ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች» (ኢሳ. 7፡14) በማለት፣ ነቢዩ ሚክያስም መሲሑ በቤተ ልሔም እንደሚወለድ (ሚክ. 5፡2) በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናግረዋል። ነቢያቱ ተስፋውን ለማየት በጾምና በጸሎት ሲማጸኑ እንደኖሩ ሁሉ፣ ቅዱስ ጳውሎስም በሐዲስ ኪዳን «ዘመኑ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን... ልጁን ላከ» (ገላ. 4፡4) በማለት የትንቢቱን ፍጻሜ አብስሯል። ምዕመናንም በዚህ ፆም የነቢያትን የተስፋና የናፍቆት መንፈስ በመካፈል፣ የክርስቶስን መምጣት በልባቸው እየተጠባበቁ ይቆያሉ።

‎

‎​የቅዱሳን አበው አስተምህሮ የፆመ ነቢያትን ጥልቅ መንፈሳዊ ምሥጢር በሚገባ ያብራራል። ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ «እውነተኛ ጾም ማለት ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት መራቅ ነው፤ አፍ ሲጾም ዓይን፣ ጆሮና ልብም ከክፉ ነገር መጾም አለባቸው» በማለት ያስተምራል። ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ እና ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊም በድርሳናቶቻቸው አምላክ ሰው የሆነው ሰውን አምላክ ለማድረግ (በጸጋ ለማክበር) እንደሆነ በመግለጽ፣ የልደት በዓል ዝግጅት ልብን ለክርስቶስ ማደሪያነት ማንጻት እንደሆነ ያሳስባሉ። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በድጓው «ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት» እያለ የወልድን ከሰማየ ሰማያት መውረድና የነቢያትን ሐሴት በጣዕመ ዜማ አስተምሯል።


‎

‎​በዘመናችን ካለው ፈጣንና በቁሳዊ ሩጫ ከተሞላ ሕይወት ጋር ስናዋሕደው፣ ፆመ ነቢያት ለዘመኑ ሰው ታላቅ መንፈሳዊ ዕረፍትና የውስጥ መረጋጋት የሚሰጥ ወቅት ነው። ዛሬ የገና በዓል በማለት በብዙዎች ዘንድ በገበያ ግርግር፣ በልብስና በምግብ ዝግጅት ብቻ የሚታሰብበት አዝማሚያ ቢታይም፣ ፆመ ነቢያት ግን ከዚህ ጫጫታ ወጥተን ራሳችንን እንድንመረምር ይጋብዘናል። በዚህ ወቅት ምዕመናን ከእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች (ሥጋ፣ ወተት፣ ቅቤ፣ እንቁላል) በመከልከል፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ጾም አድረው በመመገብ እንዲሁም ቅዳሜና እሑድን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በማክበር ሥጋዊ ፈቃዳቸውን ይገዛሉ። ከዚህም ባለፈ በዘመናዊው ዓለም የበዛውን የማኅበራዊ ሚዲያና የአሉታዊ መረጃ ሱስ በመቀነስ፣ በጸሎት፣ በንስሐ እና በዘመኑ ችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች በመመጽወት የቤተ ልሔምን ትሕትና እና የክርስቶስን ፍቅር በተግባር የምንገልጥበት ሕያው ትምህርት ቤት ሊሆን ይገባል።


‎

‎ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝበ ክርስቲያን፣ ለቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረ ሰብ፣ ለመምህራን፣ ለሠራተኞችና ለተማሪዎች፣ እንዲሁም ለደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት፤ ጾመ ነቢያትን በሰላም፣ በጤናና በመንፈሳዊ ደስታ እንድንጀምር ያደረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው።


‎

‎አባ ፊልጶስ (ዶ/ር)

‎የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ኃላፊ/ፕሬዝደንት የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

_______________________________



In the name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, one God. Amen.


‎

‎"Is not this the fast that I choose: to loose the bonds of wickedness, to undo the straps of the yoke, to let the oppressed go free, and to break every yoke? Is it not to share your bread with the hungry and bring the homeless poor into your house; when you see the naked, to cover him, and not to hide yourself from your own flesh?" (Isaiah 58:6–7)


‎

‎The Fast of the Prophets (Yegena Tsom) is one of the seven great feasts of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, a time of great blessing when believers welcome the birth of Jesus Christ through prayer, repentance, and spiritual preparation. This fast begins on November 24th of each year and lasts until January 7th, culminating in the celebration of the birth of our Lord Jesus Christ (Yegena Fast), which is celebrated on January 7.


‎

‎​The main reason why the fast is called “Fast of the Prophets” is because it commemorates the time when the Old Testament prophets prophesied in advance the birth of the Messiah and the work of salvation for mankind, and awaited it with longing and prayer. The prophet Isaiah said, “Behold, a virgin shall conceive, and bear a son, and shall call his name Immanuel” (Isa. 7:14), and the prophet Micah, guided by the Holy Spirit, said that the Messiah would be born in Bethlehem (Mic. 5:2). Just as the prophets prayed and prayed in fasting and prayer to see their hope fulfilled, Saint Paul also announced the fulfillment of the prophecy in the New Testament, saying, “When the fullness of time had come, God sent forth his Son, born of a woman” (Gal. 4:4). The faithful, sharing in the spirit of hope and longing of the prophets during this fast, await the coming of Christ in their hearts.

‎

‎The teaching of the holy fathers clearly explains the deep spiritual mystery of the fasting of the prophets. The great Father of the Church, Saint John Afework, said, “True fasting means not only abstaining from food but also abstaining from sin; "When the mouth fasts, the eyes, ears, and heart must also fast from evil." St. Cyril of Alexandria and St. Ephrem the Syrian, in their sermons, both emphasize that the preparation for the Nativity is to purify the heart for the dwelling of Christ, stating that God became man in order to make man God (to glorify him with grace). The Ethiopian scholar St. Yared, in his sermon, also taught the descent of the Son from the heavens and the joy of the prophets with a sweet melody, saying, "The Son descended from heaven into the heavens, and the joy of the prophets." When we combine it with the fast and materialistic life of our time, the Fast of the Prophets is a time that gives great spiritual rest and inner peace to the people of our time. Although many people today tend to think of Christmas only in terms of the hustle and bustle of the market, clothes, and food preparations, the Fast of the Prophets invites us to step out of this noise and examine ourselves.

‎

‎During this time, believers control their carnal desires by abstaining from animal products (meat, milk, butter, eggs), fasting from Monday to Friday, and observing church services on Saturday and Sunday. Furthermore, by reducing the addiction to social media and negative information that is prevalent in the modern world, and by praying, repenting, and interceding for those in need, it should be a living school where we can demonstrate the humility of Bethlehem and the love of Christ in practice.

‎

‎To the faithful of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, to the community of Holy Trinity University, its teachers, staff, and students, and to the dioceses of the South Omo and Ari Zones: glory and thanks be to our God, who has brought us to begin the Fast of the Prophets in peace, health, and spiritual joy.


‎

‎Abba Philipos (Dr.)

‎President of Holy Trinity University Archbishop of the South Omo and Ari Zones Diocese

More Stories

Our Latest Publishings

Holy Trinity University

Holy Trinity
University

The Orthodox Theology is the experience of the communion opened by Jesus Christ, affirming the truth of teaching about the mystical communion, fundamental to knowing God.

Legal

Contact

Addis Ababa, Ethiopia
+251 111 233 528+251 111 233 528
president-office@htu.edu.et

Newsletter

Stay updated with our latest news, events, and academic publications.

Š 2026 Holy Trinity University. All rights reserved.

A ministry of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church