ለክቡር ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ገብረሐና ገብረጻድቅ ሽኝት ተደረገላቸው


____

(ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ/ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም)


ለርቀትና ኢለርኒንግ (E-Learning) ኮሌጅ ዲን ለነበሩት ክቡር ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ገብረሐና ገብረጻድቅ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው የበላይ ሓላፊ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በተገኙበት ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ ወደሚሔዱበት አገር በጎ አገልግሎት እንዲገጥማቸው በመመኘት ሽኝት ተደረገላቸው። 


በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አንጋፋ መምህራንና ሠራተኞች "ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ገብረሐና ገብረጻድቅ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና በሓላፊነት ሲያገለግሉ ብቁ መምህርና መካሪ አባት ናቸው" ብለዋል። የዩኒቨርሲቲውን ሠራተኛና መምህራን ወክለው አስተያየት የሰጡት መምህራን "እንዲህ ያሉትን በትምህርት ዝግጅትም በሕይወትም የተሻለ ልምድና ብቃት ያላቸውን መምህራን መሸኘት ከባድ ቢሆንም የተላኩት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት በመሆኑ በአገልግሎት መንፈስ እንዳልተለዩን እናምናለን" ብለዋል።


ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ገብረሐና ገብረጻድቅ ለተደረገላቸው የሽኚትና የምስጋና መርሐ ግብር ከብርና ምስጋና አለኝ በማለት ንግግር የጀመሩ ሲሆን ብዙ ቦታ አገልግያለሁ እንዲዚህ ዩኒቨርሲቲ ግን በአገልግሎት የረካሁበት ተቋም አልገጠመኝም በማለት ተሰናብተዋል።


ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የዩኒቨርሲቲው የበላይ ሓላፊ ፕሬዚደንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቃለ ምዕዳናቸው "ለአንዲት ቤተክርስቲያን አገልግሎት ወደ ውጪ ቢሔዱም ዩኒቨርሲቲያችን ሩቅ ላሉ መምህራንም በሩ ክፍት ሆኖ በኢለርኒንግ (E-Learning) ትምህርት እየሰጠ በመሆኑ ባሉበት የዩኒቨርሲቲው አካል ሆነው ያገለግሉናል" በማለት መመሪያ ሰጥተዋቸዋል። ዩኒቨርሲቲው በሓላፊነት በሰጠዎት የርቀትና ኢለርኒንግ ኮሌጅ የሚዳሰስ ለውጥ ማምጣታቸውን የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ርቀትና ኢለርኒንግ ኮሌጅ ከዚህ በኋላ መሥመር ይዟልና ብዙ አያደክመንም ብለዋል።


 á‰Ľáá‹•áŠá‰łá‰¸á‹ የምዕራቡ ዓለም ለአገልግሎት ዕንቅፋት ቢኖረውም በትጋት ራሱን ለሚያሳድግ ሰው ግን ምቹ የትምህርት ማእከል ነው በማለት ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ ወደ ስፍራው ሊሔዱ ሽኝት የተደረገላቸው ሊቀ ኅሩያን አባ ገብረሐና ገብረጻድቅን ትምህርታቸውን በጥብቅ እንዲከታተሉ አባታዊ ምክር ሰጥተው የእጅ መስቀል በስጦታ አበርክተውላቸዋል።


በሽኚት መርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ ስጦታዎች የተበረከቱላቸው ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ፕ/ር አባ ኃይለገብርኤል ግርማ፣ የአስተዳደር ምክትል ፕሬዚደንት መልአከ ኃይል አባ ጽጌድንግል ፈንታሁን፣ የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ረ/ፕ ግርማ ባቱ፣ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችና መምህራን ተገኝተዋል።


የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

Latest News And Anouncments

Our latest Publishings

Holy Trinity University

The Orthdox Theology is the experiance of the communion that opend by Jesus Christ and affirm the truth of teaching about the mystical communion, which is fundamental to knowing of God.

Social