← Back to Press Center
OTHERSACTIVE2026-10-22

ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል:: (ዮሐ. 11፥25)

ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል:: (ዮሐ. 11፥25)


የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ዕረፍት በሰማንበት በዚህ የሐዘን ወቅት፤ በትንሣኤና በዘላለማዊ ሕይወት ተስፋ ላይ ተመሥርተን ያለንን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ፤ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለመላው ምእመናን መጽናናትን እንመኛለን።


ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የአገልግሎት ኀላፊነቶች በታማኝነት በማገልገል፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ አንድነትና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ አባት ነበሩ። በተለይም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በመሆንና በተለያዩ አህጉረ ስብከቶች በኖላዊነት በሰጡት አባታዊ አገልግሎት፣ በጸሎታቸው፣ በትጋታቸውና ለቤተ ክርስቲያናችን ባላቸው ፍቅር የሚታወሱ ናቸው።


ብፁዕነታቸው በቅርብ ዓመታት ያጋጠማቸውን የጤና እክል እየተቋቋሙ በአገልግሎታቸው ያሳዩት ቁርጠኝነት የአገልጋይነታቸውን ክብርና የእምነታቸውን ጽናት የሚመሰክር ነው። በዘመናቸው የተወጡት ኀላፊነትና ያበረከቱት መንፈሳዊ አስተዋጽኦ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክና በሁሉም ምእመናን ልብ ውስጥ ሲታወስ የሚኖር ነው።


ሞት የምድራዊ ጉዞ መጨረሻ ቢሆንም፣ በክርስቶስ ለሚያምኑ ግን የትንሣኤ ተስፋ አለ። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ «ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ» በማለት የሰጠን ቃል በሐዘናችን መካከል የመጽናናትና የተስፋ ምንጭ ነው። ስለዚህ የብፁዕነታቸውን መለየት በጥልቅ ሐዘን እያሰብን፣ በእምነትና በትንሣኤ ተስፋ ተጽናንተን ነፍሳቸውን በሰላም እንዲያሳርፍ ወደ እግዚአብሔር እየጸለይን፥ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረ ሰብ፣ በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ስም ለብፁዕነታቸው ወዳጅ ዘመዶች፣ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለመላው የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ያለንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፣ እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።


የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን!


ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር)

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት

የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

More Stories

Our Latest Publishings

Holy Trinity University

Holy Trinity
University

The Orthodox Theology is the experience of the communion opened by Jesus Christ, affirming the truth of teaching about the mystical communion, fundamental to knowing God.

Legal

Contact

Addis Ababa, Ethiopia
+251 111 233 528+251 111 233 528
president-office@htu.edu.et

Newsletter

Stay updated with our latest news, events, and academic publications.

Š 2026 Holy Trinity University. All rights reserved.

A ministry of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church