← Back to Press Center
ANNOUNCEMENTACTIVE2026-11-13

ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በድሬደዋ ሀገረ ስብከት!

ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በድሬደዋ ሀገረ ስብከት!



(ቅ.ሥ.ዩ. ኅዳር 2፣ 2019 ዓ.ም)


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና ትውልድን በመንፈሳዊነትና በዕውቀት የሚያገለግሉ አገልጋዮችንና ምዕመናንን ለማፍራት፣ የነገረ መለኮት ትምህርትን ለማስፋፋት በዋናው ግቢ በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንቱ መጨረሻ እንዲሁም በርቀትና በይነ-መረብ ትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪና ሁለተኛ ዲግሪ ከ7,500 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። 


የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት እያሳየ ካለው ሁለንተናዊ ተቋማዊ እድገት በተጨማሪ የኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ትምህርትን በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ በያዘው ዕቅድ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጉባኤ የርቀት እና በይነ-መረብ ትምህርት ኮሌጅ ከዚህ ቀደም በወላይታ እና ጅማ አኅጉረ ስብከት ከከፈታቸው የርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ማዕከላት በተጨማሪ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድሬደዋ፣ በደሴ፣ በባህር ዳር እና በአዳማ አጥንቶ አዳዲስ ቅርንጫፍ ማዕከላት እንዲከፈቱ ውሳኔ አስተላልፏል።


በዚህም ውሳኔ መሠረት የርቀት እና በይነ-መረብ ትምህርት ኮሌጅ በቅርቡ በይፋ ምዝገባ የሚጀመርበት የደሴ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ማዕከል እንደተጠበቀ ሆኖ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በከፈተው የርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ማዕከል በዛሬው ዕለት 02/03/2019 ዓ.ም የኮሌጁ ዲን በተገኙበት በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል።


ከኮሌጁ ያገኘነው ቀዳሚ መረጃ እንደሚያሳየው የቅርንጫፍ ማዕከላቱ እየተከፈቱና እየተስፋፉ ያሉት በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፣ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬና የሥራ መመሪያ ሰጪነት ነው።

More Stories

Our Latest Publishings

Holy Trinity University

Holy Trinity
University

The Orthodox Theology is the experience of the communion opened by Jesus Christ, affirming the truth of teaching about the mystical communion, fundamental to knowing God.

Legal

Contact

Addis Ababa, Ethiopia
+251 111 233 528+251 111 233 528
president-office@htu.edu.et

Newsletter

Stay updated with our latest news, events, and academic publications.

Š 2026 Holy Trinity University. All rights reserved.

A ministry of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church