በሞሮኮ የመሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ ሓላፊ ዶ/ር መሐመድ ረፊቅ የተመራ ልዑክ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሙዚየምንና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲን ገበኘ

በሞሮኮ የመሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ ሓላፊ ዶ/ር መሐመድ ረፊቅ የተመራ ልዑክ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሙዚየምንና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲን ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጎበኘ።


በጉብኝቱ ወቅት ለልዑካኑ ገለጻ የሰጡት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ á‰¤á‰°áŠ­áˆ­áˆľá‰˛á‹ŤáŠ— በሃይማኖታዊ፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አስተምህሮ ትውልዱን በማነጽ፤ በትምህርትና በሌሎች የልማት ዘርፎች በስፋት በመሳተፍ እያከናወነች ያለው ተግባር ለመላው አፍሪካ መልካም ተሞክሮ የሚሆን ስለሆነ ከቤተክርስቲያናችን ልምድ ወስዶ መተግበር ለዕድገትና ሥልጣኔ ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡


በሞሮኮ የመሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ ሓላፊና የልዑካኑ መሪ ዶ/ር መሐመድ ረፊቅ በበኩላቸው “አፍሪካዊያን የነበረንን ቀደምት ሥልጣኔ እና ልምዶቻችንን ቀምረን፤ ትብብራችንን አጠናክረን በጋራ ሠርተን ለትውልድ የሚሻገር ታሪክ መሥራት አለብን፤ ከዛሬው ጉብኝትም በርካታ ትምህርትና ልምድ ወስደናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ልዑካኑን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ገለጻ ከሰጡ በኋላ የሀገራችንና የቤተክርስቲያናችንን ጥንታዊ ሥልጣኔ የሚያሳዩ ሥጦታዎችና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጻሕፍትን በስጦታ አበርክተዋል። 


የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት

Latest News And Anouncments

Our latest Publishings

Holy Trinity University

The Orthdox Theology is the experiance of the communion that opend by Jesus Christ and affirm the truth of teaching about the mystical communion, which is fundamental to knowing of God.

Social