የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችና መምህራን የብፁዕ አቡነ ፊልጶስን አስተዳደር አመሰገኑ

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችና መምህራን ትናንት የካቲት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ/ፕሬዚዳንት እና የደቡበ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስጋና መርሐ ግብር አዘጋጅተዋል። የዩኒቨርሲቲው ሓላፊዎችና መምህራን ይህን የምስጋና መርሐ ግብር ያዘጋጁት ብፁዕነታቸው እየሰጡት ባለው አስተዳደር በመደሰታቸውና የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሥርዓት ለአሠራር ቀላልና ግልጽ በመሆን ሁሉንም አሳታፊ እየሆነ በመምጣቱ ነው ብለዋል። 


በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ፕ/ር አባ ኃይለ ገብርኤል በተለያዩ ዓለማት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያገለገልኩ ሲሆን በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ አማካይነት ወደ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተጠርቼ አገልግሎት ሥጀምር ያየሁት የተለየ ነገር ነው። ይኸውም ብፁዕነታቸው ለሓላፊዎች የሚሰጡት የአስተዳደር ነጻነትና ቀጥተኛ ውሳኔያቸው ነው ብለዋል። 


የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ምክትል ፕሬዚደንት መልአከ ኃይል አባ ጽጌድንግል ፈንታሁን በበኩላቸው ብፁዕ አባታችን የቤተክርስቲያን ልጅነትን ብቻ የሚመለከቱ ደገኛ አባት ናቸው በማለት ለዚህም የእኔ አመጣጥ ምስክር áˆ˜áˆ†áŠ• ይችላል ብለዋል።  


ከብፁዕነታቸው ጋራ በተለያየ ዘመን አብረው የሠሩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ሓላፊነት የሚሠሩና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጋራ መሥራት በነጻነት ማገልገል እንደሆነና ብፁዕነታቸው ያዩትን ስሕተት የሚያርሙ áŒ áŠ•áŠŤáˆŤá‹áŠ• ጎን የሚያበረታቱ ቸር እረኛ መሆናቸውን መስክረዋል። ብፁዕነታቸው በአካዳሚክ፣ በአስተዳደርና በልማት ዩኒቨርሲቲውን ለመለወጥ ከሠራተኞች ጋራ ተግባብተው á‰€áŠ•áŠ“ ሌሊት የሚተጉ የመሪነት ምሳሌ መሆናቸውንም መስክረዋል።


የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ለብፁዕነታቸው የተለያዩ ሥጦታዎችን ያበረከቱ ሲሆን ብፁዕነታቸውም እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች አይገቡኝም የተሠራው ሥራ ሁሉ እናንተ የሠራችሁትና እናንተን ይዤ የሠራሁት ነው ብለዋል። ምናልባት ወደፊት እንድሠራ እያበረታታችሁኝ ከሆነ ከዛሬ ይልቅ ነገ የተሻለ ለመሥራት አነሣሥታችሁኛል ያሉት ብፁዕነታቸው ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርጌ እናንተን የመሰሉ ልጆቼን ይዤ የተሻለ ሥራ ለመሠራት ብርታትና ጉልበት እንደሚኖረኝ አረጋግጫለሁ።


በመርሐ ግብሩ ላይ ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ዋና ሼል አስኪያጅ፣ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ á‹¨áŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹Ť ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን áˆ•áŒťáŠ“ቾና ቤተሰብ á‹ľáˆ­áŒ…ቾ ዋና ሼል አስፈጻሚ፣ ቀሲስ ኢ/ር ሱራፌል ተዘራ á‹¨áŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹Ť ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምግባረ ሠናይ ሆስፒታል ዋና ሼል áŠ áˆľáˆáŒťáˆšáŁ ሊቀ ማእምራን ዮሐንስ ለማ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቨርጂኒያ ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሃብተ ማርያም ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መምህር እና ሌሎቸም ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን á‹¨áˆáˆł ግብዣ፣ የቅኔ፣ የዝማሬ እንዲሁም መርሐ ግብሩ የተዘጋጀበትን ምክንያት የተመለከተ አጫጭር ንግግሮች ቀርበዋል፡፡


የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት

Latest News And Anouncments

Our latest Publishings

Holy Trinity University

The Orthdox Theology is the experiance of the communion that opend by Jesus Christ and affirm the truth of teaching about the mystical communion, which is fundamental to knowing of God.

Social