ለመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር አመልካቾች የመግቢያ መስፈርት
1.የዘመናዊ ትምህርት ውጤትን በተመለከተ
1.1. የትምህርት ሚኒስቴር የሚያዘጋጀውን የኹለተኛ ዯረጃ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዶ በእንግሊዝኛ እና በሒሳብ ትምህርት ቢያንስ C ያለው፣ በጠቅላላ በአምስት የትምህርት ዓይነቶች በመሰናዶ ትምህርት ወዯ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት የሚያስችለው ነጥብ ያለው ወይም በ12ኛ ክፍል ሒሳብንና እንግሊዝኛን ጨምሮ 2 ነጥብና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው ወይም Level IV ያለው እና የብቃት ማረጋገጫ (Certificates of Competency – COC) ማቅረብ የሚችል፤
1.2. አመልካቹ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማረበትን ውጤት የሚገልጽ የውጤት መግለጫና መሸኛወረቀት (Transcript) ዋናውንና ቅጅውን ማቅረብ የሚችል፤
1.3. የሚያቀርበው የብሔራዊ ፈተና የምስክር ወረቀት ስለትክክለኛነቱ ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት አረጋግጦ ማቅረብ የሚችል፣
1.4. በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚሰጠውን የጽሑፍና የቃል መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል፤
1.5. ከሀገረ ስብከት ወይም ከሚኖሩበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ የአባልነት ምስክር ዯብዳቤ ማቅረብ የሚችል ፤
1.6. የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የተማሪዎችን ዯንብና ሥነ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ውል የሚገባ፤
1.7. ኹለት ጉርድ 4 X 4 (Passport Size) ፎቶ ግራፍ ሙሉ ፊትና ኹለት ጆሮዎችን የሚያሳይ፤
2.ትውልዯ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ያልኾኑ አመልካቾች
2.1. አመልካቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ወይም የምሥራቅ ኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አባል መኾን አለበት፤
2.2. አመልካቹ የኹለተኛ ዯረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ መኾኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለበት አገር በሚመለከተው የትምህርት ባለሥልጣን ዕውቅና ያገኘ መኾን አለበት፤
2.3. ማንኛውም የትምህርት ማስረጃ አቻ ግመታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ ማረጋገጫ ባለሥልጣን መረጋገጥ አለበት፤
2.4. አመልካቹ ለአገሪቱና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ ለመገዛት ፈቃዯኛ መኾን አለበት፤
2.5. አመልካቹ ዩኒቨርሲቲው የሚያዘጋጀውን የጽሑፍና የቃል ፈተና ማለፍ አለበት፤
2.6. አመልካቹ ተመሳሳይ የትምህርት መስክ ከሚሰጥበት ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ከመጣ መመዝገብ ይችላል፤
2.7. አመልካቹ የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጉዳዮች መወሰኛ ጉባኤ ያዘጋጀውን መተዳዯሪያ ዯንብ የሚቀበልና የሚያከብር መኾን አለበት፤
3. ለኹለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር አመልካቾች የመግቢያ መስፈርት
3.1. አመልካቹ በትምህርተ መለኮት ከቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ወይም ተመሳሳይ የትምህርት መስክ ከሚሰጥበት ለምሳሌ በቋንቋ፣ በግእዝ፣ በሥነ ልሳን፣ በፊሎሎጂ፣ በታሪክ፣ በፍልስፍናና በማኅበራዊ ጥናት (Sociology) በመሳሰሉት ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ከመጣ መመዝገብ ይችላል፤
3.2. ማንኛውም የውጭ አገር አመልካች የመጀመሪያ ዲግሪው (BTh or BA) ዕውቅና ካለው ዩኒቨርሲቲ የተሰጠና በሚኖርበት አገር ከሚገኝ የትምህርት ባለሥልጣን ተረጋግጦ መቅረብ አለበት፤
3.3. የትምህርተ መለኮት የመጀመሪያ ዲግሪው አጠቃላይ ውጤት (Cumulative Grade) 2.75 ነጥብ እና ከዚያ በላይ መኾን አለበት፤
3.4. ዩኒቨርሲቲው የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ አለበት፤
3.5. ከቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ መዯበኛ ተማሪዎች ለኹለተኛ ዲግሪ ትምህርት ማመልከትና መመዝገብ የሚችሉት ቤተ ክርስቲያንን ቢያንስ ለኹለት ዓመት ያህል ያገለገሉ መኾናቸውን የሚያረጋግጥ ዯብዳቤ ከሚመለከተው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው ፤
3.6. አመልካቹ ከታወቁ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ወይም የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሦስት የድጋፍ ዯብዳቤዎችን ማቅረብ አለበት፤
3.7. አመልካቹ በሚኖርበት አካባቢ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል መኾኑን የሚያረጋግጥ የሰበካ ጉባኤ አባልነት ካርድ ማቅረብ አለበት፤
3.8. አመልካቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ መኾኑና ሥነ ምግባራዊ ማንነት ያለው መኾኑ በሚመለከታቸው አካላት ምስክረንት የሚረጋገጥ መኾን አለበት፤
3.9. ዋናው የውጤት መግለጫና መሸኛ ወረቀት (Official Transcript) ከተማረበት የትምህርት ተቋም ታሽጎና ማኅተም ተዯርጎበት በቀጥታ ወዯ ዩኒቨርሲቲው መላክ አለበት፤
3.10. የዩኒቨርሲቲውን ሕግና ሥርዓት የሚቀበልና የሚያከብር መኾን አለበት፤
3.11. አመልካቹ ለኹለተኛ ዲግሪ ከተመዘገበ በኋላ በመመረቂያ ጽሑፉ የሚሠራውን ጥናትና ምርምር የሚገልጽ ርእሱን፣ የምርምር ጥያቄዎቹን፣ ዓላማውንና የሚከተለውን ስልት የሚያሳይ መነሻ ሓሳብ (Concept Paper) በጽሑፍ ማቅረብ አለበት፤ ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ቁጥሮች በሥራ ቀንና ሰዓት ይዯውሉ።
+251111233528
+251111226060
ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራር ጽ/ቤት